ተልዕኮ (Mission)
በክልሉ ውስጥ የሚከሰቱ የምግብ ዋስትና እጦት ችግሮችንና መሠረታዊ መንስኤዎችን በማጥናት፣ ህብረተሰቡን በልዩ ልዩ የልማት ኘሮጀክቶችና ኘሮግራሞች በማሳተፍና የተለያዩ የልማት አጋሮችን በማስተባበር አደጋን መከላከል፣ የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ማረጋገጥና ድህነትን መቀነስ፡፡
ራዕይ / Vission
የአማራ ክልል ህዝብ አደጋን የመከላከልና የመቋቋም አቅሙ ጎልብቶ፣ የምግብ ዋስትናው ተረጋግጦ የዳበረ ልማት ተጠቃሚ ሆኖ ማየት፡፡
እሴቶች /Values/
• ተልዕኮዎቻችንን እና ራዕያችንን ለማሳካት በቁርጠኝነት እንሰራለን፤ • የአደጋ ተጋላጭነትን በመቀነስ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተግተን እንሰራለን፤ • ለአደጋ ተጋላጮች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በታማኝነት እንሰራለን፤ • ቀጣይ ዕድገትን ለማረጋገጥ የማያቋርጥ ለውጥን ባህላችን እናደርጋለን፤ • የውጤታችን መለኪያ የተገልጋዮች እርካታ ይሆናል፤ • የስራ ፍቅር፣ ከበሬታና መልካም ስነ-ምግባርን እናጐለብታለን፤ • ሴቶች፣ወጣቶችና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ ሰጥተን እንሰራለን፤ • ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት አሰራርን እንከተላለን፤ • የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን፡፡
