




በአማራ ክልል ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ በ9 ዞኖች በሚገኙ 25 ወረዳዎች የጎርፍ ቅድመ መከላከል ሥራ መሥራቱን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ።
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ምክትል ኮሚሽነር ሰርክአዲስ አታሌ እንደገለፁት፣ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል 145 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ እየተሰራ ነው።
ክረምቱን ተከትሎ የሚመጣ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል 145 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ የተለያዩ ቅድመ መከላከል ስራዎችን እያከናወንን ነው ብለዋል።


የክረምት ወራት የራሱ መልካም ፀጋዎች እንዳሉት ሁሉ መደበኛ በሆነ እና መደበኛ ባልሆነ የዝናብ መጠን ምክንያት የመሬት መንሸራተት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የወንዞች መሙላት ሊያጋጥም ይችላል ብለዋል።
ምክትል ኮሚሽነሯ አያይዘውም፤ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስትቲዩት ትንበያ እንደሚያሳየው ከሆነ በክልሉ ውስጥ በዘጠኝ ዞኖች ያሉ 25 ወረዳዎች ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸው ተለይቷል።
በዚህም ለህብረተሰቡ በቂ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ከመስጠት ጀምሮ የጎርፍ አደጋን ለመከላከል የሚረዱ ሥራዎች መሠራታቸውን አብራርተዋል።
