




የአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር መወሰኛ ረቂቅ ደንብ ዝግጅት ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣በ10ኛው መደበኛ ጉባኤው የአስፈጻሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ፣ ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅን ማጽደቁ ይታወቃል። በዚህም የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ይባል የነበረው ወደ አብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በሚል የስያሜ ለውጥ እንዲደረግ በምክር ቤቱ እና በካቢኔ እደተወሰነ የሚታወስ ጉዳይ ነው።
የመድረኩ ዓላማም ለረቂቅ ደንብ ግብዓት ማሰባሰብና መስተካከል የሚገባቸውን ጉዳዮች ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በጋራ ለማዬት ያለመ ነው። ረቂቅ ደንቡ የተዘጋጀው ከፍትህ ቢሮ፣ ከፕላንና ልማት እና ከአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በጋራ በተዋቀረ ኮሚቴ ነው።
የአብክመ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም፣ የፕላንና ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ፣ የርዕሰ መስተዳደሩ የኢኮኖሚ ዘርፍ ልማት አማካሪ የሆኑት አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ፣ የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ብርቱካንን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ተወካዮች፣ የኮሚሽኑ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ምክክር ተደርጓል።
የመድረኩ ዓላማ ለረቂቅ ደንብ ግብዓት ማሰባሰብና መስተካከል የሚገባቸውን ጉዳዮች ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በጋራ ለማዬት ያለመ ነው። ለረቂቅ ደንቡ ግብዓት የሚሆኑ በርካታና ገንቢ ሀሳቦችና አስተያዬቶች የተገኙበት መድረክ ነበር።
የማቋቋሚያ ረቂቅ ደንቡን የአቀረቡት የአርቃቂ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት የአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አማካሪ የሆኑት አቶ አንሙት በለጠ ሲሆኑ የደንቡ አስፈላጊነት፣ ጠቅላላ ድንጋጌዎች፣ ስለ ኮሚሽኑ ዓላማ፣ ስልጣንና ተግባር፣ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ምን እንደሚመስሉና ተያያዥ ጉዳዮችን በዝርዝር አቅርበዋል።
በመድረኩ ተሳታፊዎች ከቀረበው ረቂቅ ደንብ በመነሳት ተጨማሪ ግብዓት የሚሆኑና ክፍተትን የሚሞሉ ሀሳቦችን አንስተዋል።
ውይይቱን የመሩት የአብክመ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም እና የአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዲ/ን ተስፋው ባታብል ሲሆኑ በተሰጡ አስተያዬቶችና ማስተካከያዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ደንቡ በቀጣይ መስተካከልና መካተት የሚገባቸው ጉዳዮች ተደራጅተው ከታዩ በሗላ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ኮሚሽኑም የተጣለበትን ሀላፊነትና ተግባር በአግባቡ ይወጣል። ለአደጋ የማይበገር ማህበረሰብ ለመፍጠርና ለሚያጋጥሙ አደጋዎችም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚተጋ ይሆናል::
