ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች የአዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ ተደረገ።

የአብክመ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከአባይ እና ዳሽን ባንኮች ጋር በመተባበር በባህርዳር ከተማ ለሚገኙ የአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ለ173 ለሚሆኑ የቤተሰብ ሀላፊዎች ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ግራም ፊኖ ዱቄት እና 3 ሊትር ዘይት ነው።

የእንኳን አደረሳችሁ ድጋፉን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የአብክመ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፣ የአብክመ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲ/ን ተስፋው ባታብል እና የአብክመ የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ/ር) አስረክበዋል።

በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነሮች እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው የአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች የእንኳን አደረሳችሁ ድጋፉን ሰጥተዋል።

የአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖች በዓልን ደስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ ድጋፍ ላደረጉ ባንኮች ድጋፉን በሰጡ አመራሮች ምስጋና ቀርቧል።

የአብክመ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ባለፈው ዓመትም አጋር አካላትን በማስተባበር ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የበዓል መዋያ የሚሆን መሰል ድጋፍ እንዳደረገ ይታወቃል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top