






“የታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት!” በሚል መሪ ቃል የአብክመ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች በብሔራዊ ጥቅምና የጂኦ-ስትራቴጂ ቁመና ዙሪያ የፓናል ውይይት አካሂደዋል።
የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአብክመ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዲያቆን ተስፋው ባታብል ሲሆኑ ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሚናውን መጫወት አለበት ብለዋል። ብዙ ህዝብ ይዘን፣ ሰፊ የቆዳ ስፋት ያላት ሀገር እያለን የባህር በር ባለቤት አልባ መሆን የለብንም። ህዳሴ ግድብን በዲፕሎማሲያዊ ጥረታችን ተባብረን ገንብተን ጨርሰናል ያሉት ኮሚሽነሩ የባህር በር ጥያቄያችንን በማሳካት ኃያልነታችንን ማስመለስ፣ ኢኮኖሚያችንን አሳድገን የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና ሀገራችንን ማበልጸግ አለብን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ በብሔራዊ ጥቅምና የጂኦስትራቴጂ ቁመና ዙሪያ የኮሚሽኑ አማካሪ የሆኑት አቶ አንሙት በለጠ ለፓናል ተወያዮች አቅርበዋል።
ስለብሔራዊ ጥቅም፣ የብሔራዊ ጥቅም መሰረታዊ ግቦች፣ የኢትዮጵያ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ሁኔታና ብሔራዊ ጥቅም፣ የብሔራዊ ጥቅማችን ዋነኛ ፈተናዎች፣ ፈተናዎቹ በብሔራዊ ጥቅማችን ላይ ያስከተሉት ጉዳት፣ በታደሰ ቁመና አዲሱን ዘመን መዋጀት እንደሚገባ በሰነዱ ቀርቧል።
ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር ኢኮኖሚያዊ አቅማችንን ማጎልበትና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያረጋግጥ የዲፕሎማሲ አቅምን መገንባት ይገባል ተብሏል።
የመንግስት ተቋማት ጠንካራ ተቋም በመገንባት በችግሮች አለመታሰር፣ በርዕይ መጠንከር፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና ሌባውን በመቆጣጠር ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገልጿል።
እንደ ሀገር ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነትን ማሳደግ ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው።
የመንግስት ሰራተኛው በተመደበበት ቦታ ውጤታማነትን በማረጋገጥ ጠንካራ የስራ ባህል መገንባትና ቁጭት መፍጠር እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል።
የጊዜ አጠቃቀም ባህልን መቀየር እና የስራ ሰዓት አጠቃቀማችን በማስተካከል፣ አዲስ ባህል መገንባትና ሁሉም ለሰላም መስራት ይገባል።
ሰብዓዊነት ላይ እንደሚሰራ ተቋም በማሰብ ሰላምን እሴት በማድረግ ሚናን በአግባቡ መወጣት ተገቢ ነው ተብሏል።
