








የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የ6 ወራት ዕቅድ ትውውቅና የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከዞን ተጠሪ ጽ/ቤቶች፣ ከአጋር አካላትና ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር የግምገማ መድረክ አካሂዷል።
የ2017/2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ እና የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበዋል። ሌላው በመድረኩ የቀረበው በቀጣይ ወራት በትኩረት መከናወን ያለባቸው የማህበረሰብ ልማት ተግባራትና በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም በኑሮ መሰረት ማሻሻያ ዘርፍ በትኩረትና በቁርጠኝነት መከናወን ያለባቸው ስራዎች ቀርበዋል።
ከቀረቡት ሪፖርቶች በመነሳት የተለያዩ ጥያቄዎች ከመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። በካፒታል በጀት በሚከናወኑ ተግባራትና ሂደቶች፣ በኑሮ መሰረት ማሻሻያ ስራዎች፣ በምረቃና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በመድረኩ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።
የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የመጨረሻ ግብ ተጠቃሚ ደንበኞችን ህይወት በመቀየር ጥሪት አፍርተው ራሳቸውን ችለው ከተረጅነት እንዲወጡ ማድረግ ነው ተብሏል።
ውይይቱን የመሩት ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ወ/ሮ እታገኘሁ አደመ እና የምግብ ዋስትና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወርቁ ከበደ ሲሆኑ ለተነሱ ጥያቄዎችና ለተሰጡ አስተያዬቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ምክትል ኮሚሽነር እታገኘሁ አደመ ዕቅዱንና በቀሪ ወራት የሚከናወኑ ተግባራትን ከላይ እስከ ታች ያለው አካል በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። በትራንስፈር፣ የኑሮ መሰረት ማሻሻያ እና የማህበረሰብ ልማት ስራዎች ላይ በትኩረት በመስራት የተመደበው በጀት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማድረግ እንደሚጠበቅ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በፕሮግራሙ የካፒታል በጀት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች የቀረው ጊዜ አጭር በመሆኑ ከአሁኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ልቅም አድርጎ በመስራት ዝግጁ መሆን ይጠይቃል ብለዋል ኮሚሽነሯ።
የሴፍቲኔት ፕሮግራም አምስት ታህሳስ 30 ስለሚጠናቀቅ ቀሪ የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ተግባራትን በወቅቱ ለማከናወን በየደረጃው ያለ አመራርና ባለሙያን ቁርጠኝነት ይጠቃል ሲሉ አደራ ብለዋል።
የግራንትና ብድር ተጠቃሚዎች ቁጠባ እንዲቆጥቡ በማድረግና በአግባቡ የሃብት ልዬታ በማካሄድ አጸድቆ ለክልል በማሳወቅ ለምረቃ እንዲዘጋጁ ማስቻል የነገ ሳይሆን የዛሬ ተግባር በመሆኑ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
ከዚህ በፊት ተመሳሳይ መድረክ ከምስራቅ አማራ ዞኖች እና ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር እደተካሄደ የሚታወቅ ነው።
