



የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኤፍራታና ግድም ወረዳ መስቀልበር ቀበሌ ነሀሴ 2/2017 በጎርፍ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ቀይ መስቀል ቅርንጫ ማህበር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዳምጠው እምሻው እንደገለጹት ቀደም ሲል ነሀሴ 2/2017 ዝናብ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በርካታ የህብረተሰብ ህፍሎች የተጎዱ መሆኑን ከወረዳው አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና አቶ ቻለው ታደሰ በተገኙበት 600 በላይ ነዋሪዎች ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን በተደረገው ዳሰሳ ጥናት እንዳረጋገጡ ገልጸው ለ400 አበወራና እማወራ 4ሚሊየን ብር ለእያንዳንዳቸው 10 ሽህ ብር በአካውንታቸው እንደሚገባላቸው ገልጸውልናል ፡፡

አቶ ዳምጠው አያይዘው እንደገለጹት በጣም ለተጎዱ ለ200 ሰዎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ብርድ ልብስ ፤ማብሰያ ቀሳቁስ፤ ምንጣፍ፤ ቱታ ለሴቶች ቢጃማና የንጽህና መጠበቂያ፤ የውሃ ማከሚያ ክሎሪን እንዲሁም ሳሙና በቦታው በመገኘት በዛሬው እለት የወረዳው ምግብ ዋስትና አደጋ መከላከል አቶ ቻለው ታደሰ በተገኙበት ከ5ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ደጋፍ ያረጉ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡
