




የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ከኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርም ለፌደራል መጠባበቂያ እህል ክምችት በክልሎች በመተግበር ላይ የሚገኘው የቅድመ ፋይናንስ ስርአት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ የገለጹት ለክልል፣ ለከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነሮችና ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የመነጅመን አካላት ጋር የነበረውን የውይይት መድረክ በከፈቱበተ ወቅት ነው፡፡
ኮሚሽነሩ አክውም በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና በዘጠኝ ክልሎች በተገባ ውል በመተግበር የሚገኘው የፌደራል የስትራቴጂክ መጠባበቂያ ክምችት በተለያዩ ስልቶች ወደ ማምረት ስራ መገባቱን የክልል ኮሚሽነሮች በሰመራው የውይይት መድረክ ላይ ገልጸዋል።
በዚሁ የውይይት መድረክ ክልሎች ለሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ማብሰሪያ የመሸጋገሪያ ስልት (Exit Strategy) ማዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው የኮሚሽኑ የአገልግሎቶች ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌቱ ንጉሴ አስገንዝበዋል።
ከክልሎች የሚቀርቡ የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም የአፈጻጸም ሪፖርቶች ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ቢያሳይም አሁንም የጥራትና ትክክለኛነት ጉድለቶችን ማረም እንደሚገባና መንግስት በዘርፉ ለሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ለመረጃ ጥራትና ትክክለኛነት የበለጠ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ አሻግሬ ተሾመ አሳስበዋል።
የኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ አማራ፣ ትግራይና አፋር ክልሎችና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዘርፉን የአፈጻጸም ሪፖርታቸውን በማቅረብ ልምድ መለዋወጥ ያስቻለ ተሞክሯቸውን አጋርተዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያም ምክትል ኮሚሽነር ነሲቡ ያሲን የቅድመ ፋይናንስ የስትራቴጂክ መጠባበቂያ እህል ክምችት የሚተገበርበት ሞዳሊቲ፣ የምርት መጠን፣ የጥራት ደረጃው ተጠብቆ ምርቱን መች ለማስረከብ እንደተዘጋጁ ማረጋገጥ ከክልሎች እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።
ምክትል ኮሚሽነር አይድሩስ ሀሰን በበኩላቸው የክልል ኮሚሽነሮች ከክልል አመራሮቻቸው ጋር በመመካከር በየክልሎቻቸው የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ማረጋገጫ ስትራቴጂ ላይ መግባባት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
በሪፖርት አቅራቢዎችና ሌሎችም የተገኘውን ልምድና የመማማሪያው ጊዜ ብዙ መልካም ልምድ የቀሰሙበት መሆኑን በመጠቆም በሚፈለገው ጥራትና መንገድ፤ በተቀመጠለት ጊዜ የመጠባበቂያ ክምችት የመያዙን ስራ ለማከናወን የተቀመጠውን አቅጣጫ ወደ ተግባር መለወጥ ወሳኝ መሆኑን በመስማማት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተስማምተዋል፡፡
