የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እየተደረገ ነው።

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን እብናት ወረዳ የፌደራል አደጋ መከላከልና አመልድ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ እህል ድጋፍ እየተደረገ ነው።

በእብናት ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ደስታየ ከፍያለው እንደገለጹት በወረዳው የድርቅ ተጋላጭ ለሆኑ አስራ ሁለት ቀበሌዎች ከ79,000 በላይ የህ/ሰብ ክፍል የሁለት ወር ቀለብ የበቆሎና አልሚ ምግብ እህሎችን ድጋፍ እያደረግን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችም እየተደረገላቸው ላለው ድጋፍ አመስግነዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top