የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ለ19,000 ሽ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በመቀጠዋ ወረዳ የፌደራል አደጋ መከላከል ከክልሉ አደጋ መከላከል ጋር በጋራ በመሆን የተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ለ19,000 የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ እህል ድጋፍ እየተደረገ ነው።

የመቀጠዋ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አብራረው ተገኘ እንደገለጹት በወረዳው የድርቅ ተጋላጭ ለሆኑ ለ12 (አሰራ ሁለት) ቀበሌዎች 6270 (ስድስት ሽ ሁለት መቶ ሰባ) ኩንታል ለ19,000 የህብረተሰብ ክፍሎች የሁለት ወር ቀለብ የበቆሎና አልሚ ምግብ እህሎችን ድጋፍ እያደረግን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ቡድን መሪው አያይዘው እንደገለፁት ይህ ድጋፍ ለታለመለት አላማ በአግባቡ እንዲደርስ የዞን ቅደመ ማስጠንቀቂያ አመራሮችና ባለሙያዎች ላደረጉት አስተዋጽኦ በወረዳው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተፈጥሮ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችም እየተደረገላቸው ላለው ድጋፍ በማመሰገን ቀጣይነት እንዲኖረውም አሳስበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top