
በአሁኑ ጊዜ የክረምት ዝናብ መፈጠር አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮልጂ ክስተቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከሙ፣ በአንፃሩ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ እንደሚያመዝን መረጃዎች ያሳያለ፡፡ በመሆኑም በሚቀጥለት የኦክቶበር ሶስተኛዉ አሥራ አንድ ቀናት( እ.ኤ.አ.ከኦክቶበር 21-31/2025 ) የምስራቅ አማራ ዞኖች ከጥቂት የደቡብ እና የሰሜን ወሎ ስፍራዎቻቸው በስተቀር የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ እንደሚያመዝን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በሌላ በኩል የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የክረምት ወቅት ዝናብ እያገኙ የነበሩት የምዕራብ አማራ አካባቢዎች ሊይ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በፀሀይ ሀይል ታግዘውከሚጠናከሩት የደመና ክምችቶች ሊይ በመነሳት በምዕራብ አማራ አካባቢዎች በሰሜን፣ በማዕከላዊ እና በደቡብ ጎንደር፣በሰሜን ጎጃም፣ በባህር ዳር፣ በምዕራብ ጎጃም እና በአዊ ዞን ባለ ወረዳዎች ሊይ አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት በ24 ሰዓት ውስጥ ከ11 እስከ 30 ሚ.ሜ የሚደርስ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
በተጨማሪም በአንዳንድ የምስራቅ አማራ ከፍተኛ ስፍራዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከ5.0 ዲግሪ ሴሌሺየስ በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ።
