በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ያበረከታቸው አስተዋጽዎ ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ያበረከታቸው አስተዋጽዎ ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም በአማራ ብሔራዊ ክልል ያበረከታቸው አስተዋጽዎ እና ከተረጂነት ወደምርታማነት ንቅናቄ እቅድና እስካሁን በተከናወኑ ጉዳዮች ላይ ከሚዲያና ኮሚኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ለመምከር ባዘጋጀው መድረክ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል። በመድረኩ በአማራ ብሔራዊ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአቅም ግንባታና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ዘሪሁን ፍቅሩ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንገሻ ፈንታው፣ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉቀን ጸጥዬ የተቋማት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመድረኩን አስፈላጊነት በተመለከተ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአቅም ግንባታና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ዘሪሁን ፍቅሩ ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈው መድረኩን ከፍተዋል።

በመድረኩ ሁለት ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ሲሆን የልማታዊ ሴፍቲኔት ከየት ወደየት የሚለውን የሚዳስስ ጽሁፍ የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ እታገኘሁ አደመ ጽሁፉን ያቀረቡ ሲሆን በምግብ ራስን ለመቻል ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት፣ ነጻነትና ክብር በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረው የንቅናቄ እቅድ እና እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ላይ የተዘጋጀውን ጽሁፍ የኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር ሠርካዲስ አታሌ እያቀረቡ ይገኛሉ። በርዕሰጉዳዮቹ ላይ የቀጣይ የተግቦቦት ሥራዎችን የሚያመላክት ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

መጋቢት 25/2017ዓ.ም.

ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር!!!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top