በአይና ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ለተቸገሩ ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ግምት ያለው ቅድስት ምድርህን አድን ማህበር የምግብ ድጋፍ አደረገ።

በአይና ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ለተቸገሩ ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ግምት ያለው ቅድስት ምድርህን አድን ማህበር የምግብ ድጋፍ አደረገ።

=========================================

ቅድስት ምድርህን አድን ማህበር በአክሽን ኤድኢትዮዺያ የገንዘብ ድጋፍ በአይና ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ለተቸገሩ ወገኖች 4 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አደረገ።

ማህበሩ በሰሜን ወሎ ዞን አይና ቡግና ወረዳ በምግብ እጥረት ለተቸገሩ ወገኖች 3 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር ግምት ያለው 237 ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ 62 ነጥብ 5 ኩንታል አልሚ ምግብና 790 ሊትር ዘይት ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

ድጋፉን ያስረከቡት በቅድስት ምድርህን አድን ወልድያ ፕሮጀክት አስተባባሪ ይመር ካሳዬ የምግብ እህል ድጋፉን በሰሜን ወሎ ዞን አይና ቡግና ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ 525 ነፍሰ ጡርና አጥቢ እናቶች ለ500 ህፃናት እንድውል ታሰቦ የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ድጋፉም በወረዳው ለተመረጡ ሶስት ቀበሌዎች ለተመለመሉ ተጎጅዎች እንድውል እንደሚደረግና 3 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር ወጭ ተደርጎበታል ብለዋል።

ድጋፉን አመስግነው የተረከቡት የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባባሪያ ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አለሙ ይመር በአይና ቡግና ወረዳ የተከሰተው የምግብ እጥረት ለመፍታት የተቆራረጠ ቢሆንም በመንግስትና በረጅ ድርጅቶች እየቀረበ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንፃር መሰል ድጋፎች እንደሚያስፈልጉ ገልፀዋል።

የቅድስት ምድርህን አድን ማህበረም ይህን ችግር በመረዳት 3 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር ግምት ያለው ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

በወረዳው ከ109 ሺህ በላይ ማህበረሰብ የምግብ እህል ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው እና ከነዚህ ውስጥም 46 ሺህ ለሚሆኑት እናቶች አፋጣኝ የምግብ እህል እንደሚያስፈልጋቸው በጥናት ተለይቷል ብለዋል።

(ሰሜን ወሎ ኮሙኒኬሽን)

+2

All reactions:

1515

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top