“የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ጸጋዎችን ተጠቅሞ ምርት እና ምርታማነትን መጨመር ይገባል”

አደም ፋራህ

“የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ጸጋዎችን ተጠቅሞ ምርት እና ምርታማነትን መጨመር ይገባል”

አደም ፋራህ

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማሥተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ሰፋፊ የልማት ሥራዎች በውጤታማነት እየተተገበሩ መመልከታቸውን ገልጸዋል።

በከተማዋ እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በጥሩ ኹኔታ እየተሠራ መመልከታቸውን ነው የተናገሩት።

የኮሪደር ልማት ተቋማት በቅንጅት እንዲሠሩ ያስቻለ መኾኑንም ገልጸዋል። የኮሪደር ልማት ከተሞች የተዋቡ እና ለነዋሪዎች የተመቹ እንዲኾኑ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።

በባሕር ዳር ከተማ የዜጎችን የኑሮ ኹኔታ የሚያሻሽል የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን መመልከታቸውንም ተናግረዋል።

የሌማት ትሩፋት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚያስችልም ገልጸዋል። የሌማት ትሩፋት በውጤታማነት እየተገበሩ ከሚገኙ አካባቢዎች የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር አንደኛው መኾኑን ነው የተናገሩት።

በሌማት ትሩፋት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እየተፈጠረላቸው መኾኑን ገልጸዋል።

በባሕር ዳር ያለው የሌማት ትሩፋት ለከተማዋ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት አስተዋጽኦ እያበረከተ መኾኑንም ተናግረዋል።

በከተማዋ በወተት፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ በዓሳ ሃብት ልማት እና በሌሎች የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ውጤታማ ሥራዎች አሉ ነው ያሉት።

እንደ ሀገር የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ተኪ ምርትን ማምረት እና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ማምረት የሚቻለው በየአካባቢው ጸጋውን በመጠቀም ነው ብለዋል።

አሁን የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ከቀጠለ በአጭር ጊዜ ብልጽግናን ማረጋገጥ ይቻላል ነው ያሉት። ከተረጅነት በመላቀቅ የተሟላ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ይገባልም ብለዋል።

“የልማት ሥራዎች ውጤታማ ኾነው እንዲቀጥሉ ድጋፋችንን እና ክትትላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን” ነው ያሉት።

ኅብረተሰቡም እየተተገበሩ ካሉ እና ከተቀረጹ የልማት ሥራዎች ተጠቃሚ እንዲኾን ሥራዎችን መደገፍ እና የአካባቢውን ጸጋ መጠቀም አለበት ብለዋል።

ለሀገር ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገት የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክትም አስገንዝበዋል።

#አሚኮ

All reactions:

77

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top