ኮሚሽኑ በተግዳሮቶች ውስጥ ሆኖ የተሻለ አፈጻጸም አስመዝግቧል:ዲ/ን ተስፋው ባታብል (ኮሚሽነር)

የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በቀን 07/12/2017 ዓ/ም ከሰራተኞች ጋር አካሂዷል።

በመድረኩም ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ እያለፈም ቢሆን የተሻለ የዕቅድ አፈጻጸም እዳስመዘገበ ተገልጿል።

የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ዲያቆን ተስፋው ባታብል መድረኩን ሲከፍቱ እደተናገሩት በ2017 በጀት ዓመት ኮሚሽኑ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖ በርካታ ተግባራትን በውጤታማነት ፈጽሟል ብለዋል።

የግምገማዊ ውይይቱ ዓላማም ባሳለፍነው በጀት ዓመት በጥንካሬና በውጤታማነት የተመዘገቡ ተግባራትን ለማስቀጠል እና በድክመት የታዩ አፈጻጸሞችን ለማሻሻል የጋራ ለማድረግና የቀጣይ አቅጣጫ በጋራ ለመያዝ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኮሚሽኑ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር በአቶ ማናዬ አማርኸኝ ቀርቧል። በሪፖርቱም የቁልፍ እና አበይት ተግባራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በጥንካሬና በድክመት ተለይቶ በዝርዝር ቀርቧል።

ከቀረበው ሪፖርት በመነሳት ከሰራተኞቹ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዋል፣ ልዩ ልዩ የሆኑ አስተያዬቶች ተሰጠዋል። የውይይት መድረኩን የመሩት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር የሆኑት ዲያቆን ተስፋው እና ምክትል ኮሚሽነር ሰርክአዲስ አታሌ ሲሆኑ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያዬቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እያንዳንዱ የኮሚሽኑ ስኬት የመላ ሰራተኞች ትጋትና ድካም ውጤት ነው ያሉት ምክትል ኮሚሽነር ሰርክአዲስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየታለፈ ዘርፈ ብዙ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል።

ከዕቅዱ ጀምሮ ኦረንቴሽን እስከመስጠት እና በየጊዜው እየተከለሱ፣ በጥብቅ ድጋፍና ክትትል የተመራበት በጀት ዓመት እንደነበር ተናግረዋል። በቀጣይ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገርና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተጀመረውን ተግባር በትኩረት መከታተልና መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዕቅዱ በውጤታማነት እንዲፈጸም ጥብቅ የሆነ የድጋፍና ክትትል ስርዓት ከክልል እስከ ወረዳ ተዘርግቶ የተሰራበት እንደነበር አንስተው በቀጣይ አዲስ በጀት ዓመትም በትኩረት በሚከናወኑ ስራዎች ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጠው መድረኩ ተጠናቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top