በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተፈናቅለው በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ1 ሚሊዮን 72 ሺህ ብር ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ።

በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተፈናቅለው በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ1ሚሊዮን 72ሺህ ብር ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

=================================

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደረጀ አለማየሁ እንደገለፁት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በነበረው ፀጥታ ችግር ምክንያት የሰዎች መፈናቀልና ንብረት ውድመት በደረሰበት ወቅት ጀምረው ከወረዳው ከተቋቋመ ቴክኒክ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን በርካታ መረጃዎችን ሲያሰባሰቡና ሲያደራጁ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

አክለውም ሃላፊው ለ1066 በላይ ለሆኑ ግለሰቦች 160 ኩንታል ስንዴ ለ7 ቀበሌ ማህበረሰብ ለ1 ሰው 15 ኪሎ ስንዴ ድጋፋ መደረጉን አስታወቁ።

ይህንን ድጋፋ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ያደረገው የራሳችንን ችግር በራሳችን ለመሸፈን በተያዘው እቅድ መሠረት ከወረዳው አርሶ አደሮች የተሰበሰበ ስንዴ መሆኑንም ገልጸዋል። በቀጣይም በወጣው ፕሮግራም መሠረት ለሌሎች ቀበሌዎችም የሚያሰራጩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም በወረዳው የተቋቋመው ኮሚቴዎችም በየጊዜው የሚሰበሰበውን ሀብት ለጉዳቱ ተካፋይ ለሆኑ የቀበሌ ማህበረሰቦች ፍትሃዊ በሆነ አግባብ ሲያሰራጩ መቆየታቸውንና ለወደፊት የሚሰበሰቡ ሀብቶችን ለማሰራጨት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

እርዳታ የተደረገላቸው አካላትም በዚህ ወቅት የምግብ እህል በመሰጠቱ ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀው ራሳችንን እስክንችል ድረስ ድጋፋችሁ አይለየን ብለዋል።

ሞረትና ጅሩ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን

▶️Facebook:- www.facebook.com/profile.php?id=100067131507069

▶️TELEGRAM:- https://t.me/dpfspcc

▶️TWITTER/X account/:-https://x.com/disaster_food_1

▶️Youtube:- https://www.youtube.com/@DPFSC

▶️Tiktok:-https://www.tiktok.com/@dpfsc

1 thought on “በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተፈናቅለው በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ1 ሚሊዮን 72 ሺህ ብር ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ ተደርጎላቸዋል ።”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top