


በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ሲሆን ለዚህም ኢንሸቲቭ አገልግሎት እዲዉል የተለየዉን 40ሄ/ር ሄክታር መሬት ታርሶ በማሽላ 23.5ሄ/ር ፣በሩዝ 1.5 ሄ/ር እና በማሾ 15ሄ/ር እስካሁን በዘር ተሸፍኗል።
ከዚህ በተጨማሪም ላለፏት አመታት በነበረ ግጭት ሳይታረሱ የቀሩ መሬቶችን ከአጎራባች የኦረሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አመራሮች እና ማህበረሰቦች ጋር በመመካከር እና በመደጋገፍ ወደ ምርት ስራ ማህበረሰቡ እንዲገባ እየተደረገ ያለዉ ትልቅ ስራ ሊደነቅ ይገባል።
ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ፤ለተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነት እና ክብር![]()
