የሴፍቲኔት ፕሮግራም ስር በሰደደ የምግብ መታጣትና በከፋ ችግር ውስጥ የሚገኙ ተጠቃሚዎችን ህይወት አሻሽሏል፣ ጥሪት እንዲገነቡ አስችሏል፡ ወ/ሮ እታገኘሁ አደመ (ምክትል ኮሚሽነር)

የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም አምስት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት ማለትም በ02/12/2017 ዓ/ም የክልሉ ስትሪንግ ኮሚቴ አባል ከሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት፣ ከዞን ተጠሪ ጽ/ቤቶች እና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በባህርዳር ተካሂዷል።

ግምገማዊ መድረኩን ያስጀመሩት የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ወ/ሮ እታገኘሁ አደመ የመድረኩ ዓላማ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ውጤታማነቱንና ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ በጋራ ለመገምገም ነው ብለዋል።

የ2017 በጀት ዓመት በርካታ የፕሮግራሙ ተግባራት በውጤታማነት የተከናወኑበት፣ የክልሉ ስትሪንግ ኮሚቴ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የመራበት እንደነበር ገልጸዋል።

ሴፍቲኔት በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ከከፋ ድህነት ያወጣና እርዳታን ከልማት ጋር በማስተሳሰር ተጠቃሚዎች የኑሮ መሰረታቸው እንዲሻሻል ያስቻለ ውጤታማ የመንግስት ፕሮግራም ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩም በማህበረሰብ ልማት የተከናወኑ ተግባራት፣ በኑሮ መሰረት ማ

ሻሻያ ተግባራት የተከናወኑ ተግባራት፣ የፕሮግራሙ በጀት አጠቃቀምን የሚያሳይ እና አጠቃላይ በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የሚያሳዩ ሪፖርቶች ቀርበዋል።

ከቀረቡት ሪፖርቶች በመነሳት በመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያዬቶች እየተነሱ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ባለፉት ዓመታት ስር በሰደደ የምግብ መታጣትና በከፋ ችግር ውስጥ የነበሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ህይወት ከማሻሻል አልፎ ቋሚ ጥሪት እንዲገነቡ ያስቻለ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።

የፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሆኑና የነጻ ድጋፍ ተጠቃሚዎች ከተረጅነት አስተሳሰብ መውጣት እንዳለባቸው ተነስቷል። ተረጂዎች በተፈጠረላቸው ጥሪት በአግባቡ በመጠቀም ከፕሮግራሙ ተመርቀው እንዲወጡና በዘላቂነት የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ተብሏል በመድረኩ።

የማጠቃለያ ውይይቱን የመሩት የአብክመ ግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ አት ደረጀ ማንደፍሮ እና ምክትል ኮሚሽነር እታገኘሁ አደመ ሲሆኑ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያዬቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጧል።

በመጨረሻም አቶ ደረጀ (የግብርና ቢሮ ምክትል ሀላፊ) በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው መቀጠል አንዳለባቸው አቅጣጫ ሰጥተው፤ የነበሩ ችግሮች ትምህርት ሊወሰድባቸው እንደሚገባ አስገንዝበው ግምገማዊ ውይይቱ ተጠናቋል።

የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም አምስት በ11 ዞኖች በ87 ወረዳዎች እና በ1823 ቀበሌዎች እየተተገበረ የሚገኝ ውጤታማ ፕሮግራም ነው። ባሳለፋቸው አምስት ምዕራፎች የተራቆቱ ተራሮችንና መሬቶች አልብሷል፣ ወረዳን ከወረዳ፣ ቀበሌን ከቀበሌ መንገዶችንና ድልድዮችን በመስራት አገናኝቷል፣ ት/ቤቶችን ገንብቷል፣ ጤና ጣቢያዎችን ገንብቷል፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ተቋማትን፣ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማዕከላትን ገንብቷል፣ የመስኖ ግድቦችን፣ ካናሎችን፣ የማህበረሰብ ኩሬዎችን ሰርቷል፣ የማህበረሰብ ተፋሰስ ልማቶችን ያለማ በክልሉ ውስጥ አበርክቶው የጎላ የልማት ፕሮግራም ነው።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top