

በብልፅግና ፓርቲ ኢንሸቲቭ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ የሚገኘው የተረጅነት ቅነሳ/ በምግብ ራስን የመቻል ተግባር በጃማ ወረዳ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የጃማ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኃይሉ አሰፋ የተረጅነት ቅነሳ/ በምግብ ራስን የመቻል ተግባርን ስኬታማ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በዛሬው ዕለትም በ017 ቀበሌ 1 ሄ/ር መሬት በዘር የተሸፈነ ሲሆን እንደ ወረዳ እስካሁን 16.5 ሄ/ር በዘር መሸፈን መቻሉን ገልጸዋል።
በቀጣይም ተግባሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኃላፊው አመላክተዋል።
