የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የዞን ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ኦረንቴሽን አካሄደ።

የአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የዞን ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ኦረንቴሽን አካሄደ።

================================

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት አሻጋሪና ዘላቂ የልማት እቅድ ኦረንቴሽን መድረክ የዞን ተጠሪ ጽ/ቤቶች በተገኙበት አካሄዷል፡፡

2017 በጀት ዓመት አበረታች ሥራዎች የተከናወኑበት እና ውጤት የተመዘገበበት፤ በልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም የታቀዱ ፕሮጀክቶች በስኬት የተጠናቀቁበት፤ በአደጋ መከላከልና በቅድመማስጠንቀቂያና ምላሽ ሥራዎች እንዲሁም የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ የማድረግ ተግባራት በውጤታማነት የተከናወኑበት እንደሆነ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል ገልጸዋል፡፡

በችግር ውስጥ ሆነን አብዛኛው እቅዶቻችንን በስኬት ፈጽመናል፣ ዞኖችንም ወደተቀራረበ ደረጃ አምጥናል ያሉት ኮሚሽነሩ በአካል ወርዶ መስራት የሚጠይቀውን የወረዳ ፕሮፋይል ጥናት እንኳ ቴክኖሎጂን በመጠቀምና ሰፋ ያለ የሰው ኃይል መድቦ በማሰራት ከእቅድ በላይ ማከናወን ከመቻሉም በላይ የእውቀት ሽግግር ያደረግንበት ተግባር መሆኑ፤ ከተረጂነት አስተሳሰብ በመላቀቅ በምግብ ራስን ለመቻል በተጀመረው ኢኒሼቲቭ ላይ በየደረጃው በርካታ መድረኮችን በማካሄድ አስተሳሰቡን ለማስረጽ ሰፊ ሥራ መሰራቱ፣ የተፈናቃይን መረጃ ከማጥራትና ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም አኳያ የተሰሩ ሥራዎች የሚበረታቱና ለቀጣይ ዓመትም አጠናክረን ልናከናውናቸው ይገባል ብለዋል፡፡

የ2017 በጀት ዓመትን አፈጻጸም፣ ከ5 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅድና ከክልሉ አሻጋሪና ዘላቂ ልማት እቅድ የተቀዳው የኮሚሽኑ የ2018 በጀት ዓመት እቅድ በእቅድና በጀት ዝግጅትና ክ/ግ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማናዬ አማርኸኝ ቀርቦ በዞን ተ/ጽ/ቤቶች ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበት ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመጨረሻም በእቅዱ ላይ እስከታችኛው መዋቅር መግባባት እየተፈጠረበት እንዲፈጸም የጋራ በማድረግ በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ ለፈጸሙ አካላት የእውቅና ፕሮግራም ተከናውኖ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top