የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ጸ/ቤቶችና ፈጻሚዎች እውቅና ሰጠ

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በ2017 በጀት አመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዞን ተጠሪ ጽ/ቤቶች፣ ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች እውቅና ሰጠ።

በእውቅና መርሀግብሩ በ2017 በጀት ዓመት የሥራ ቡድኖችንና ባለሙያዎችን በማስተባበርና በዓመቱ የታቀዱ ተግባራትን በማሳካት ባስመዘገቡት ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ከዞን ተጠሪ ጽ/ቤቶች 1ኛ ደረጃ ያገኘው የሰሜን ሸዋ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት የሞተር ሳይክል ተሸላሚ ሲሆን የእውቅና ሰርተፊኬትና ዋንጫ ተበርክቶለታል፡፡ 2ኛ ደረጃ ያገኘው የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ሲሆን ዴስክቶፕ ከነፕሪንተሩና ላፕቶፕ ተሸልሟል፣ የእውቅና ሰርተፊኬትም ተበርክቶለታል፡፡ 3ኛ ደረጃ ያገኘው የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ነው፤ የዴስክቶፕና ላፕቶፕ ተሸላሚ ሆኗል፡ የእውቅና ሰርተፊኬትም ተበርክቶለታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በኮሚሽኑ ካሉ ዳይሬክቶሬቶች የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ የምግብ ዋስትና ዳይሬክቶሬት 1ኛ ደረጃ በማግኘት ዋንጫውን ወስዷል፡፡

በመድረኩ በሥራ አፈጻጸማቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ዳይሬክተሮች፣ የሥራ ቡድኖች፣ ባለሙያዎችና በተቋሙ ከመደበኛ ተግባራቸው የተለየ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ልዩ ተሸላሚዎችም የእውቅና ሰርተፊኬትና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የማበረታቻ ሽልማቱን ያበረከቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በጋራ ሲሆን በማጠቃለያው ለሁሉም ተሸላሚዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል በርካቶችን መሸለምና እውቅና መስጠት የቀጣይ ዓመት ፍላጎታችን ነው፤ ጠንክረን ህዝባችንን ልናገለግልና ከዘንድሮው በላይ ውጤት ልናስመዘግብ ይገባል ብለው የጀመርነውን የ2018 በጀት ዓመት እቅድ በላቀ ደረጃ ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ በማሳሰብ መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top