በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጃዊ ወረዳ በተለያዩ የፀጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ ከ2ሽ 5 መቶ በላይ ለማህበረሰብ ክፍሎች የምግብ እህል ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ።

በጽ/ቤቱ የቅድመ ማሰጠንቀቂያ ፈጣን ምላሽ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አንሙት ጋሹ እንደተናገሩት ከሆነ ተፈናቃዩች ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢና በእኛ ወረዳም ከባጉሳ ማሪያምና እና ባጉሳ ሽመል እግር የተፈናቀሉ ሲሆን ቁጥራቸውም 2ሽ 5 መቶ 82 አባወራና እና እማወራ ተፈናቃዩች መኖራቸውን ገልፀው በቤተሰብ ደረጃም 1ሽ 920 ቤተሰቦች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንና ከዚህ በፊትም ለጊዜአዊ መጠለያነት የሚያገለግል ከ160 በላይ ሽራ ድጋፍ መድረጉን ተናግረው አሁን ላይ መንግስት ለተፈናቀዩች እያደረገው ያለውም ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን 3 ሚሊዩን 316ሽ 600 ብር እንደሚገመትም ገልፀው የምግብ እህሉን ለተፈናቃዩች የማሰራጨቱ ስራም አስከ መስከረም 9/2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የድጋፍ ተጠቃሚ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች አስተያየታቸውን እንደሰጡት ከሆነ አሁን ላይ መንግስት እያደረገ ያለው የምግብ እህል ድጋፍ ጥሩ ቢሆንም በቀጣይ ከመንግስት ተረጅነት እንደንላቀቅና ራሳችንን እንደንችል በዘላቂነት እንዲያቋቁመንና ወደ ነበርንበት አካባቢ እንድንመለስ እና በራሳችን አምርተን እንደንኖር ቢያደርገን የሚል አስተያየታቸውን ሰጠዋል።

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ባዘዘው በበኩላቸው በተለያዩ የፀጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው በወረዳው ለሚገኙ ተፈናቃዩች ከዚህ በፊትም የምግብ እህልም እና ሌሎች መሰል ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን አሁን ላይም ወረዳው ከክልሉ መንግስት በድጋፍ መልክ ያገኘነውን በቆሎ ለተፈናቃዩች በፍትህዊ መንገድ እያሰራጨ መሆኑን ገልፀዋል።

ሃላፊው አክለውም ተፈናቃዩች ከመንግስት ብቻ እንዳይጠብቁ የወረዳው አስተዳደር ምክር ቤት ከጣና በለስ ፕሮጀክት ጋር በመነጋገርና በመወያየት 909 አባወራዎችን በማደራጀት በጊዜዊነት ከፕሮጀክቱ መሬት በመውሰድ ወደ እርሻ እንዲገቡና የሩዝ ምርት እንዲያመርቱም የማድረግ ስራ የተሰራ ሲሆን ለተፈናቀዩችም በዘላቂነት ለማቋቋምና ወደ ነበሩበት አካባቢ ለመመለስ የተረጋጋ ኑሮ እንዲመሰርቱም ለማድረግ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገር ለጉዳዩ ትኩርት ሰጥተን እየሰራን ነው ብለዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top