





የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በባህርዳር ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ልጆች አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ በሚል ያሰባሰበውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ኮሚሽኑ ድጋፍ ያደረገው ለሰባ (70) ተማሪዎች የሚሆን ሰባ ደርዘን ደብተር እና አስራ ሰባት (17) ፓኮ እስክርቢቶ ነው።
የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ወ/ሮ ሰርክአዲስ አታሌ ወላጆች በተገኙበት ድጋፉን አስረክበዋል።
