የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጎርፍ መጥለቅለቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች አስፈላጊው ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ ፡፡

በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ በጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አስታውቋል ፡፡

በወረዳው ውስጥ በጎርፍ ለተጠቁ የድባ ፣የሻጋ እና የአቧኮኪት ቀበሌ አባወራዎች ከዚህ ቀደም የምግብ ነክ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በዚህኛው ዙር የአልባሣት፣ ልዩ ልዩ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ተጎጅዎቹ በሰጡት አስተያየት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ እንስሳቶቻቸውና የቤት ውስጥ መገልገያ እቃወቻቸው ጉዳት ስለደረሰባቸው ከድጋፉ የአገኟቸው መገልገያ ቁሣቁሶች ተጠቃሚ ስለሆኑ ለጋሽ ድርጅቱን አመስግነዋል::

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top