በተያዘዉ ጥቅምት ወር በሚኖር እርጥበት ምክንያት የሰብል በሽታዎች ሊከሰቱ የሚችሉ በመሆኑ ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለጋዜጣ ፕላስ በላከዉ የሚቲዎሮሎጂ ትንበያ እንዳስታወቀዉ፤ በጥቅምት ወር በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የሚጠበቀው ቀጣይነት ያለው ርጥበት በፍሬ በመሙላት ላይ ለሚገኙ፣ ዘግይተው ለተዘሩና በተለያየ የዕድገት ደረጃ ላይ ለሚገኙ የመኸር ሰብሎች አወንታዊ ጎን ይኖረዋል።
ሆኖም ግን በወሩ የሚኖረው ርጥበት እንደ ዋግ የመሳሰሉ የሰብል በሽታዎች እንዲከሰቱ ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር ስለሚችል አርሶ አደሮችና የሚመለከታቸው አካላት የማሳ ጉብኝት በማድረግ ምልክቶች ሲታዩ አፈጣኝ ርመጃ ለመውሰድ የሚያሰችል ዝግጅት ማደረግ እንደሚኖርባቸዉ አስጠንቅቋል።
በተጨማሪም አልፎ አልፎ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ በአንዳንድ ስፍራዎች ላይ የሚጠበቀው ከፍተኛ እርጥበት በተለይም በደረሱ ሰብሎች ላይ አሉታው ተፅእኖ የሚኖረው በመሆኑ የደረሱ ሰብሎችን ባሉት ደረቅ ሰሞናት መሰብሰብ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ዘገባው የጋዜጣ ፕላስ ነው
