በ2017 በጀት ዓመት የፕሮግራሙ የበጀት አጠቃቀምና የተግባራት አፈጻጸም የተሻለና ውጤት የተመዘገበበት ነበር:ምክትል ኮሚሽነር እታገኘሁ አደመ

የ2018 በጀት የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የ6 ወራት ዕቅድ ትውውቅ እና የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ የምዕራብ አማራ ዞኖችና የሚመለከታቸው ተቋማት በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የቀድሞው የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን በአሁኑ አጠራር የአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ወ/ሮ እታገኘሁ አደመ ሲሆኑ የፕሮግራሙን የ6 ወራት ዕቅድ ማስተዋወቅና የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ምን ይመስል እንደነበር በጋራ በጋራ ገምግሞ የጋራ አቅጣጫ ለመያዝ ያለመ መድረክ ነው ብለዋል።

ምክትል ኮሚሽነር እታገኘሁ በ2017 በጀት ዓመት የፕሮግራሙ የበጀት አጠቃቀምና የተግባራት አፈጻጸም እንደ ክልል የተሻለና ውጤታማ ነበር። በዚህም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአጠቃላይ አፈጻጸም የላቀና አመርቂ ውጤት ያስመዘገብንበት ዓመት ነበር ሲሉ ተደምጠዋል።

በዚህ 6 ወራት በፕሮግራሙ የሚከናወኑ ተግባራት በትኩረት ተይዘው እንደተለመደው በውጤት የተጀበ እንዲሆን አሳስበዋል። በቀጣይ በፕሮግራሙ የካፒታል በጀት የሚከናወኑ ተግባራት ከአሁኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተጠናቀው በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የሚለቀቀው በጀት ለታለመለት ዓላማና ተግባር በማዋልና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር በውጤታማነት መፈጸም እንደሚገባ በአጽንኦት ተናግረዋል።

በቀጣይ ሃብት አፍርተው እንዲመረቁ የተለዩት የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎችን በተያዘው ዕቅድ እክከ ታህሳስ ሰላሳ ለማስመረቅ ትኩረት ተሰጦ እንዲከናወን አሳስበዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top