




የአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP Integrated development solution for IDPs project ) ጋር በመተባበር በተፈናቃዮች መረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓት (Internal Displaced People Information Management System) ዙሪያ በምዕራብ አማራ ለሚገኙ ዞንና ወረዳ ባለሙያዎችና ቡድን መሪዎች ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው ኮሚሽኑ ከባህርዳር እና ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲዮች ጋር በመተባበር ባስለማው የዳታ ቤዝ ሶፍትዌር ዙሪያ ሲሆን ዓላማውም የተፈናቃዮችን (IDPs) መረጃ አያያዝና አስተዳደር ከነበረው ልማዳዊ አሰራር በመውጣት ዲጅታላይዝ በማድረግ ትክክለኛ፣ ተከታታይና ወጥነት ያለው መረጃ አሰባሰብን በማረጋገጥ ስህተቶችንና ድግግሞሽን በየትኛውም ቦታ ለመቀነስ ብሎም ማስወገድ ነው።
በዋናነት በተፈናቃይ የመረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓቱ ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ ዓላማው እና በሚያስገኘው ጥቅም ዙሪያ በሶፍትዌር ባለሙያ በሆኑት በአቶ ሀይለየሱስ አባተ ስልጠናው። ወደ ስርዓቱ የተፈናቃይ መረጃ እንዴት ማስገባት፣ ማስተዳደርና መተንተን እንዴት እንደሚቻል የተግባር ስልጠና ተሰጧል።

አዲሱ የመረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓት በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃዮች መረጃ በአንድ ማዕከል እንዲገኝ ከማድረጉም በላይ በቀላሉ ለማስተዳደር፣ በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማሰራጨት እና ለውሳኔ ሰጪ አካላት በፍጥነት ርምጃ እንዲወስዱ ያግዛል።
ከአጋር አካላት ጋር ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ያሻሽላል፣ የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን ያቀላል፣ የወረቀትና የማኑዋል ስራዎች እንዲሁም የሪፖርት መዘግዬቶችን ያስቀራል። ከምንም በላይ የተፈናቃዮች መረጃ አያያዝ ጥራት እንዲኖረውና ለማንኛውም አካል ግልጽነት ያለው መረጃ ይሰጣል ተብሏል።
