ሙስናና ብልሹ አሰራርን መታገል ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ በመሆኑ በጋራ መታገል ያስፈልጋል:ዲ/ን ተስፋው ባታብል (ኮሚሽነር)

የአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን “ትዉልድን በሥነ ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!” በሚል መሪ መልዕክት በፓናል ውይይት አክብረዋል።

ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ22ኛ ጊዜ ፣ በሀገራችንና በክልላችን ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር የሆኑት ዲ/ን ተስፋው ባታብል ሲሆኑ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች በሀገራችን ብሎም በክልላችን በህዝባችን ላይ የሚያደርሰውን ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ ቀውስ ለመከላከልና ለማስቆም ከህብረተሰቡ ጋር በአንድነት ለመታገል በማሰብ በዓሉን ማክበር እንዳስፈለገ ገልጸዋል።

ሙስናና ብልሹ አሰራርን መታገል ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ በመሆኑ በጋራ መታገል ያስፈልጋል ነው ያሉት ኮሚሽነሩ። በትውልድ ስነምግባር ግንባታ ላይ መስራት፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመንና ተጠያቂነትን በማስፈን ሙስናን በጋራ መከላከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ለማክበር የተዘጋጀ ሰነድ በአቶ ደረጀ ሽፈራው (በኮሚሽኑ የውስጥ ኦዲት ባለሙያ) ቀርቦ በመድረኩም ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች እየተነሱ ውይይት ተካሂዷል።

ሙስና በባህሪው ውስብስብ ከመሆኑ አንፃር ሳይከሰት ቀድሞ መከላከል ተመራጭ እና አዋጭው ስልት መሆኑ ተነስቷል። ተቋሙ ያስቀመጣቸው የአሰራር ስርዓቶች ሳይሸራረፉ እየተተገበሩ መሆኑን በየጊዜው ማረጋገጥ እንደሚገባ በፓናሉ ላይ የተነሳ ሌላው ጉዳይ ነው፡፡

ውይይቱን የመሩት ዲ/ን ተስፋው ባታብል ሲሆኑ ከፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያዬቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሙስና ከአስተሳሰብ ይጀምራል፣ መልካም ስነ ምግባር የተላበሰና ህጋዊ የአሠራር ስርዓት የሚከተል የስራ መሪ እና ሠራተኛ መፍጠር ተገቢ ነው፡፡

ኮሚሽኑ በህግና በመመሪያ ከተሰጡት ተግባራት በዋናነት የአደጋ ስጋት ቅነሳ ተግባራትን ማከናወን፣ ለሚደርሱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት፣ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን ሃብት የማሰባሰብና የመጠባበቂያ ክምችትን ማሳደግ ሲሆን ከብልሽት የጸዳ አገልግሎት መሥጠት ያስፈልጓል ተብሏል።
“ትዉልድን በሥነ ምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!”
26/03/2018

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top