ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል ሁሉም በጋራ መስራት ያስፈልጋል ተባለ

የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ የፀረ ጸታዊ ጥቃትን / ነጭ ሪባን ቀን / አስመልክቶ “ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ!!” በሚል መሪ ቃል ከኮሚሽኑ ሠራተኞች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለጹት ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል ሁሉም አጠናክሮ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መንስኤዎች ጉዳቶች ፣ የኢኮኖሚ ጥገኝነት፣ ሥነ- ልቦናዊና ማሕበራዊ ችግሮች የሚፈፀሙ የኃይል ጥቃቶች የሚደርሱት ከሌሎችም በርካታ ምክንያቶች የሚመነጩ ናቸው። እነዚህን ችግሮች ለመቋቋም ከአስተሳሰብ ጀምሮ መስራት ይገባናል ብለዋል። ፆታዊ ጥቃትና ፈተናዎቻቸው በአሁኑ ስዓት በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በሀገራችንም በየጊዜው እያጋጠሙ ባሉት ግጭቶች እና ጦርነቶች ምክንያት ፆታዊ ጥቃት እየጨመረ እየመጣ እንደሆነ በገለጻቸው አንስተዋል፡፡

የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌታ ለተሳታፊዎች ሲሆኑ፣ በቀረበው ጽሁፍ ላይ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዷል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር የሆኑት ዲያቆን ተስፋው ባታብል የውይይት መድረኩን መርተውታል፡፡ ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች የቀረበው የመወያያ ሰነድ ግንዛቤ የያዝንበት ሲሆን ከእኛ ተቋም አንጻር ከታች ካለው ማህበረሰብ ጋር የምንሠራ ስለሆነ በእያንዳንዱ ስራ አካተን በመተግበር ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የእቅዳችን አካል በማድረግ የምንተገብረው ይሆናል ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top